ሁሉም ሱራዎች

ሱራ 90

The City

سُورَةُ البَلَدِ

Al-Balad · መካኛ

ቁልፎች፡ ጄ ቀጣይ አያህ · K የቀድሞ አያህ

ኦዲዮ
  1. 1

    بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ لَآ أُقْسِمُ بِهَٰذَا ٱلْبَلَدِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Laaa uqsimu bihaazal balad

    በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡

  2. 2

    وَأَنتَ حِلٌّۢ بِهَٰذَا ٱلْبَلَدِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa anta hillum bihaazal balad

    አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡

  3. 3

    وَوَالِدٍۢ وَمَا وَلَدَ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa waalidinw wa maa walad

    በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡

  4. 4

    لَقَدْ خَلَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ فِى كَبَدٍ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Laqad khalaqnal insaana fee kabad

    ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡

  5. 5

    أَيَحْسَبُ أَن لَّن يَقْدِرَ عَلَيْهِ أَحَدٌۭ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Ayahsabu al-lai yaqdira 'alaihi ahad

    በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን?

  6. 6

    يَقُولُ أَهْلَكْتُ مَالًۭا لُّبَدًا

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Yaqoolu ahlaktu maalal lubadaa

    «ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡

  7. 7

    أَيَحْسَبُ أَن لَّمْ يَرَهُۥٓ أَحَدٌ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Ayahsabu al lam yarahooo ahad

    አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን?

  8. 8

    أَلَمْ نَجْعَل لَّهُۥ عَيْنَيْنِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Alam naj'al lahoo 'aynayn

    ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን?

  9. 9

    وَلِسَانًۭا وَشَفَتَيْنِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa lisaananw wa shafatayn

    ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡

  10. 10

    وَهَدَيْنَٰهُ ٱلنَّجْدَيْنِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa hadaynaahun najdayn

    ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?

  11. 11

    فَلَا ٱقْتَحَمَ ٱلْعَقَبَةَ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Falaq tahamal-'aqabah

    ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡

  12. 12

    وَمَآ أَدْرَىٰكَ مَا ٱلْعَقَبَةُ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa maaa adraaka mal'aqabah

    ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?

  13. 13

    فَكُّ رَقَبَةٍ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Fakku raqabah

    (እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡

  14. 14

    أَوْ إِطْعَٰمٌۭ فِى يَوْمٍۢ ذِى مَسْغَبَةٍۢ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Aw it'aamun fee yawmin zee masghabah

    ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡

  15. 15

    يَتِيمًۭا ذَا مَقْرَبَةٍ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Yateeman zaa maqrabah

    የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤

  16. 16

    أَوْ مِسْكِينًۭا ذَا مَتْرَبَةٍۢ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Aw miskeenan zaa matrabah

    ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡

  17. 17

    ثُمَّ كَانَ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَتَوَاصَوْا۟ بِٱلصَّبْرِ وَتَوَاصَوْا۟ بِٱلْمَرْحَمَةِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Summa kaana minal lazeena aamanoo wa tawaasaw bissabri wa tawaasaw bilmarhamah

    (ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡

  18. 18

    أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْمَيْمَنَةِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Ulaaa'ika As-haabul maimanah

    እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡

  19. 19

    وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا هُمْ أَصْحَٰبُ ٱلْمَشْـَٔمَةِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wallazeena kafaroo bi aayaatinaa hum as-haabul Mash'amah

    እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡

  20. 20

    عَلَيْهِمْ نَارٌۭ مُّؤْصَدَةٌۢ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Alaihim naarum mu'sadah

    በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡

የትርጉም እትም፦ am.sadiq

የቁጥር ድምጽ፡ ሚሻሪ ራሺድ አላፋሲ (128kbps via islamic.network CDN)።

ጽሑፍ እና ትርጉሞች፡ api.alquran.cloud · ኡትማኒ አረብኛ።

የአያህ ትርጉም ግልጽ ካልሆነ፣ ብቁ የሆነ አስተማሪን ጠይቅ - በተለይ ለህግ እና ለእምነት ጉዳዮች።

The City — Islam Word