ቁልፎች፡ ጄ ቀጣይ አያህ · K የቀድሞ አያህ
- 1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلْبُرُوجِ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wassamaaa'i zaatil burooj
የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡
- 2
وَٱلْيَوْمِ ٱلْمَوْعُودِ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wal yawmil maw'ood
በተቀጠረው ቀንም፤
- 3
وَشَاهِدٍۢ وَمَشْهُودٍۢ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa shaahidinw wa mashhood
በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡
- 4
قُتِلَ أَصْحَٰبُ ٱلْأُخْدُودِ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Qutila as haabul ukhdood
የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡
- 5
ٱلنَّارِ ذَاتِ ٱلْوَقُودِ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Annaari zaatil waqood
የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡
- 6
إِذْ هُمْ عَلَيْهَا قُعُودٌۭ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Iz hum 'alaihaa qu'ood
እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡
- 7
وَهُمْ عَلَىٰ مَا يَفْعَلُونَ بِٱلْمُؤْمِنِينَ شُهُودٌۭ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa hum 'alaa maa yaf'aloona bilmu 'mineena shuhood
እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡
- 8
وَمَا نَقَمُوا۟ مِنْهُمْ إِلَّآ أَن يُؤْمِنُوا۟ بِٱللَّهِ ٱلْعَزِيزِ ٱلْحَمِيدِ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa maa naqamoo minhum illaaa aiyu'minoo billaahil 'azeezil Hameed
ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡
- 9
ٱلَّذِى لَهُۥ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ شَهِيدٌ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Allazee lahoo mulkus samaawaati wal ard; wallaahu 'alaa kulli shai 'in Shaheed
በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡
- 10
إِنَّ ٱلَّذِينَ فَتَنُوا۟ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا۟ فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ ٱلْحَرِيقِ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Innal lazeena fatanul mu'mineena wal mu'minaati summa lam yatooboo falahum 'azaabu Jahannama wa lahum 'azaabul hareeq
እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡
- 11
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمْ جَنَّٰتٌۭ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ ۚ ذَٰلِكَ ٱلْفَوْزُ ٱلْكَبِيرُ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Innal lazeena aamanoo wa 'amilus saalihaati lahum Jannaatun tajree min tahtihal anhaar; zaalikal fawzul kabeer
እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡
- 12
إِنَّ بَطْشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Inna batsha Rabbika lashadeed
የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡
- 13
إِنَّهُۥ هُوَ يُبْدِئُ وَيُعِيدُ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Innahoo Huwa yubdi'u wa yu'eed
እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡
- 14
وَهُوَ ٱلْغَفُورُ ٱلْوَدُودُ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa Huwal Ghafoorul Wadood
እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡
- 15
ذُو ٱلْعَرْشِ ٱلْمَجِيدُ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Zul 'Arshil Majeed
የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡
- 16
فَعَّالٌۭ لِّمَا يُرِيدُ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Fa' 'aalul limaa yureed
የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡
- 17
هَلْ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ٱلْجُنُودِ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Hal ataaka hadeesul junood
የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን?
- 18
فِرْعَوْنَ وَثَمُودَ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Fir'awna wa Samood
የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡
- 19
بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فِى تَكْذِيبٍۢ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Balil lazeena kafaroo fee takzeeb
በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡
- 20
وَٱللَّهُ مِن وَرَآئِهِم مُّحِيطٌۢ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wallaahu minw waraaa'ihim muheet
አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡
- 21
بَلْ هُوَ قُرْءَانٌۭ مَّجِيدٌۭ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Bal huwa Quraanum Majeed
ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
- 22
فِى لَوْحٍۢ مَّحْفُوظٍۭ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Fee Lawhim Mahfooz
የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡
የትርጉም እትም፦ am.sadiq
የቁጥር ድምጽ፡ ሚሻሪ ራሺድ አላፋሲ (128kbps via islamic.network CDN)።
ጽሑፍ እና ትርጉሞች፡ api.alquran.cloud · ኡትማኒ አረብኛ።
የአያህ ትርጉም ግልጽ ካልሆነ፣ ብቁ የሆነ አስተማሪን ጠይቅ - በተለይ ለህግ እና ለእምነት ጉዳዮች።