ሁሉም ሱራዎች

ሱራ 81

The Overthrowing

سُورَةُ التَّكۡوِيرِ

At-Takwir · መካኛ

ቁልፎች፡ ጄ ቀጣይ አያህ · K የቀድሞ አያህ

ኦዲዮ
  1. 1

    بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ إِذَا ٱلشَّمْسُ كُوِّرَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Izash shamsu kuwwirat

    ፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤

  2. 2

    وَإِذَا ٱلنُّجُومُ ٱنكَدَرَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa izan nujoomun kadarat

    ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤

  3. 3

    وَإِذَا ٱلْجِبَالُ سُيِّرَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa izal jibaalu suyyirat

    ተራራዎችም በተነዱ ጊዜ፤

  4. 4

    وَإِذَا ٱلْعِشَارُ عُطِّلَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa izal 'ishaaru 'uttilat

    የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ፤

  5. 5

    وَإِذَا ٱلْوُحُوشُ حُشِرَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa izal wuhooshu hushirat

    እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፤

  6. 6

    وَإِذَا ٱلْبِحَارُ سُجِّرَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa izal bihaaru sujjirat

    ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤

  7. 7

    وَإِذَا ٱلنُّفُوسُ زُوِّجَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa izan nufoosu zuwwijat

    ነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ፤

  8. 8

    وَإِذَا ٱلْمَوْءُۥدَةُ سُئِلَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa izal maw'oodatu su'ilat

    በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤

  9. 9

    بِأَىِّ ذَنۢبٍۢ قُتِلَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Bi ayyi zambin qutilat

    በምን ወንጀል እንደ ተገደለች፤

  10. 10

    وَإِذَا ٱلصُّحُفُ نُشِرَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa izas suhufu nushirat

    ጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤

  11. 11

    وَإِذَا ٱلسَّمَآءُ كُشِطَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa izas samaaa'u kushitat

    ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤

  12. 12

    وَإِذَا ٱلْجَحِيمُ سُعِّرَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa izal jaheemu su'-'irat

    ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤

  13. 13

    وَإِذَا ٱلْجَنَّةُ أُزْلِفَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa izal jannatu uzlifat

    ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤

  14. 14

    عَلِمَتْ نَفْسٌۭ مَّآ أَحْضَرَتْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: 'Alimat nafsum maaa ahdarat

    ነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤

  15. 15

    فَلَآ أُقْسِمُ بِٱلْخُنَّسِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Falaaa uqsimu bil khunnas

    ተመላሾችም በኾኑት (ዐዋድያት) እምላለሁ፡፡

  16. 16

    ٱلْجَوَارِ ٱلْكُنَّسِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Al jawaaril kunnas

    ኺያጆች ገቢዎች በኾኑት (ከዋክብት)፡፡

  17. 17

    وَٱلَّيْلِ إِذَا عَسْعَسَ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wallaili izaa 'as'as

    በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤

  18. 18

    وَٱلصُّبْحِ إِذَا تَنَفَّسَ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wassubhi izaa tanaffas

    በንጋቱም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)፡፡

  19. 19

    إِنَّهُۥ لَقَوْلُ رَسُولٍۢ كَرِيمٍۢ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Innahoo laqawlu rasoolin kareem

    እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡

  20. 20

    ذِى قُوَّةٍ عِندَ ذِى ٱلْعَرْشِ مَكِينٍۢ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Zee quwwatin 'inda zil 'arshi makeen

    የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡

  21. 21

    مُّطَاعٍۢ ثَمَّ أَمِينٍۢ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Mutaa'in samma ameen

    በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡

  22. 22

    وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍۢ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa maa saahibukum bimajnoon

    ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡

  23. 23

    وَلَقَدْ رَءَاهُ بِٱلْأُفُقِ ٱلْمُبِينِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa laqad ra aahu bilufuqil mubeen

    በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡

  24. 24

    وَمَا هُوَ عَلَى ٱلْغَيْبِ بِضَنِينٍۢ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa maa huwa 'alal ghaibi bidaneen

    እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡

  25. 25

    وَمَا هُوَ بِقَوْلِ شَيْطَٰنٍۢ رَّجِيمٍۢ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa maa huwa biqawli shaitaanir rajeem

    እርሱም (ቁርኣን) የእርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም፡፡

  26. 26

    فَأَيْنَ تَذْهَبُونَ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Fa ayna tazhaboon

    ታዲያ ወዴት ትኼዳላችሁ?

  27. 27

    إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌۭ لِّلْعَٰلَمِينَ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: In huwa illaa zikrul lil'aalameen

    እርሱ የዓለማት መገሠጫ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡

  28. 28

    لِمَن شَآءَ مِنكُمْ أَن يَسْتَقِيمَ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Liman shaaa'a minkum ai yastaqeem

    ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)፡፡

  29. 29

    وَمَا تَشَآءُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa maa tashaaa'oona illaaa ai yashaaa 'al laahu Rabbul 'Aalameen

    የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡

የትርጉም እትም፦ am.sadiq

የቁጥር ድምጽ፡ ሚሻሪ ራሺድ አላፋሲ (128kbps via islamic.network CDN)።

ጽሑፍ እና ትርጉሞች፡ api.alquran.cloud · ኡትማኒ አረብኛ።

የአያህ ትርጉም ግልጽ ካልሆነ፣ ብቁ የሆነ አስተማሪን ጠይቅ - በተለይ ለህግ እና ለእምነት ጉዳዮች።