ቁልፎች፡ ጄ ቀጣይ አያህ · K የቀድሞ አያህ
- 1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ إِذَا زُلْزِلَتِ ٱلْأَرْضُ زِلْزَالَهَا
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Izaa zul zilatil ardu zil zaalaha
ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤
- 2
وَأَخْرَجَتِ ٱلْأَرْضُ أَثْقَالَهَا
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa akh rajatil ardu athqaalaha
ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤
- 3
وَقَالَ ٱلْإِنسَٰنُ مَا لَهَا
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa qaalal insaanu ma laha
ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤
- 4
يَوْمَئِذٍۢ تُحَدِّثُ أَخْبَارَهَا
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Yawmaa izin tuhad dithu akhbaaraha
በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡
- 5
بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَىٰ لَهَا
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Bi-anna rabbaka awhaa laha
ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡
- 6
يَوْمَئِذٍۢ يَصْدُرُ ٱلنَّاسُ أَشْتَاتًۭا لِّيُرَوْا۟ أَعْمَٰلَهُمْ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Yawma iziy yas durun naasu ash tatal liyuraw a'maalahum
በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡
- 7
فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًۭا يَرَهُۥ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Famaiy ya'mal mithqala zarratin khai raiy-yarah
የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡
- 8
وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍۢ شَرًّۭا يَرَهُۥ
በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Wa maiy-y'amal mithqala zarratin sharraiy-yarah
የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡
የትርጉም እትም፦ am.sadiq
የቁጥር ድምጽ፡ ሚሻሪ ራሺድ አላፋሲ (128kbps via islamic.network CDN)።
ጽሑፍ እና ትርጉሞች፡ api.alquran.cloud · ኡትማኒ አረብኛ።
የአያህ ትርጉም ግልጽ ካልሆነ፣ ብቁ የሆነ አስተማሪን ጠይቅ - በተለይ ለህግ እና ለእምነት ጉዳዮች።