ሁሉም ሱራዎች

ሱራ 96

The Clot

سُورَةُ العَلَقِ

Al-Alaq · መካኛ

ቁልፎች፡ ጄ ቀጣይ አያህ · K የቀድሞ አያህ

ኦዲዮ
  1. 1

    بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ٱقْرَأْ بِٱسْمِ رَبِّكَ ٱلَّذِى خَلَقَ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Iqra bismi rab bikal lazee khalaq

    አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡

  2. 2

    خَلَقَ ٱلْإِنسَٰنَ مِنْ عَلَقٍ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Khalaqal insaana min 'alaq

    ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡

  3. 3

    ٱقْرَأْ وَرَبُّكَ ٱلْأَكْرَمُ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Iqra wa rab bukal akram

    አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤

  4. 4

    ٱلَّذِى عَلَّمَ بِٱلْقَلَمِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Al lazee 'allama bil qalam

    ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡

  5. 5

    عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: 'Al lamal insaana ma lam y'alam

    ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡

  6. 6

    كَلَّآ إِنَّ ٱلْإِنسَٰنَ لَيَطْغَىٰٓ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Kallaa innal insaana layatghaa

    በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡

  7. 7

    أَن رَّءَاهُ ٱسْتَغْنَىٰٓ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Ar-ra aahus taghnaa

    ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡

  8. 8

    إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلرُّجْعَىٰٓ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Innna ilaa rabbikar ruj'aa

    መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡

  9. 9

    أَرَءَيْتَ ٱلَّذِى يَنْهَىٰ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Ara-aital lazee yanhaa

    አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡

  10. 10

    عَبْدًا إِذَا صَلَّىٰٓ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: 'Abdan iza sallaa

    ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤

  11. 11

    أَرَءَيْتَ إِن كَانَ عَلَى ٱلْهُدَىٰٓ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Ara-aita in kana 'alal hudaa

    አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤

  12. 12

    أَوْ أَمَرَ بِٱلتَّقْوَىٰٓ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Au amara bit taqwaa

    ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤

  13. 13

    أَرَءَيْتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰٓ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Ara-aita in kaz zaba wa ta walla

    አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤

  14. 14

    أَلَمْ يَعْلَم بِأَنَّ ٱللَّهَ يَرَىٰ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Alam y'alam bi-an nal lahaa yaraa

    አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን?

  15. 15

    كَلَّا لَئِن لَّمْ يَنتَهِ لَنَسْفَعًۢا بِٱلنَّاصِيَةِ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Kalla la illam yantahi la nasfa'am bin nasiyah

    ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡

  16. 16

    نَاصِيَةٍۢ كَٰذِبَةٍ خَاطِئَةٍۢ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Nasiyatin kazi batin khaatiyah

    ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡

  17. 17

    فَلْيَدْعُ نَادِيَهُۥ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Fal yad'u naadiyah

    ሸንጎውንም ይጥራ፡፡

  18. 18

    سَنَدْعُ ٱلزَّبَانِيَةَ

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Sanad 'uz zabaaniyah

    (እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡

  19. 19

    كَلَّا لَا تُطِعْهُ وَٱسْجُدْ وَٱقْتَرِب ۩

    በቋንቋ ፊደል መጻፍ: Kalla; la tuti'hu wasjud waqtarib

    ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡

የትርጉም እትም፦ am.sadiq

የቁጥር ድምጽ፡ ሚሻሪ ራሺድ አላፋሲ (128kbps via islamic.network CDN)።

ጽሑፍ እና ትርጉሞች፡ api.alquran.cloud · ኡትማኒ አረብኛ።

የአያህ ትርጉም ግልጽ ካልሆነ፣ ብቁ የሆነ አስተማሪን ጠይቅ - በተለይ ለህግ እና ለእምነት ጉዳዮች።

The Clot — Islam Word